እንግሊዝ የብሪታኒያ ፓስፖርት ላላቸው የሆንግ ሆንግ ዜጎች ዜግነት ልትሰጥ እንደምትችል አስታወቀች፡፡

ቻይና በሆንግ ኮንግ ላይ ያወጣችውን የደህንነት ህግ ካላቆመች፤ እንግሊዝ ፓስፖርት ላላቸው የሆንግ ኮንግ ዜጎች በሃገሯ ዜግነት ለመስጠት መንገዱ እንደሚመቻች በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶሚኒክ ራብ በኩል አስታውቃለች፡፡

ራብ ይህን መግለጫ የሰጡት እንግሊዝ፣አሜሪካ፣አውስትራሊያና ካናዳ አዲሱን የቻይና የደህንነት ህግ በጋራ ማውገዛቸውን ተከትሎ ነው፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ በሆንግ ኮንግ የብሪታኒያ ፓስፖርት የያዙ 300 ሺህ ሰዎች አሉ፡፡

እነዚህ ሰዎች ያለቪዛ እንግሊዝና ራስ ገዝ አስተዳደሮቿን ለስድስት ወራት ያክል የመጎብኘት መብት አላቸው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በአባይነሽ ሽባባው
ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *