የደቡብ ክልል ከአዲስ በአበባ በመቀጠል ሌላኛው የኮሮና ቫይረስ ወረሽኝ ማዕከል እንዳይሆን ስጋት እንዳለው አስታወቀ፡፡

የክልሎ ጤና ቢሮ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳለው በአዲስ አበባ እየተደረገ ባለው የቤት ለቤት አሰሳ የተገኙ የክልሉ ነዋሪዎች ውጤታቸው ሳይደርስ ወደ ክልሉ በመመለሳቸው ምክንያት ስጋት ውስጥ መግባቱን ተናግሯል፡፡

የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ አጥናው ካውዛ ለጣቢያችን እንደተናገሩት በአዲስ አበባ በቀን ስራ ተሰማርተው የነበሩ ስድስት ወጣቶች የጤና ሚኒስቴር ቤት ለቤት ባደረገው አሰሳ ነበር ምርመራ የተደረገላቸው፡፡

ይሁን እንጂ በከተማዋ የኮሮና ቫይረስ ያመጣውን የስራ መቀዛቀዝ ተከትሉ ስራ በማጣታቸው ውጤታቸው ሳይደርስ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በዚህ መሀል ታዲያ ከፍተኛ መዛመት ሳደርስ እንዳልቀረ ስጋት እንዳለው ይናገራሉ፡፡

ወጣቶቹ ውጤታቸው በቫይረሱ መያዛቸውን ስለሚያመለክት በአፋጣኝ ወደ ህክምናው እንዲገቡ ቢፈለጉ መገኘት ስላልቻሉ ጤና ሚኒስቴር በላከልን መረጃ መሰረት ተከታትለን አምስቱን አግኝተናል አንዱ ግን ስልኩን አጥፍቷል ፤የሰጠው መረጃም ስህተት በመሆኑ ማግኘት አልቻልንም ብለዋል አቶ አጥናው፡፡

በደቡብ ክልል እስካሁን በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው ሰዎች ቁጥር አሁን ወደ 13 ከፍ ብሏል።

ስድስት ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመው ወጥተዋል፡፡

አቶ አቅናው እንደሚሉት ቤት ለቤት ምርመራው የሚደረግበትን መንገድ ማሻሻል እንደሚገባ የሚያሳይ ክስተት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሁን የተገኙት ሰዎች የጤና ሚኒስቴር የናሙና ምርመራን ሲያደርግ መረጃዎች በትክክል በመመዝገቡ መሆኑን የሚያስረዱት አቶ አቅናው ምርመራ ሳይደረግላቸው ስራ በማጣት ወደ ትውልድ ስፍራቸው የሚመለሱ በርካታ የክልሉ ሰዎች እንዳሉ ያነሳሉ።

ትናንት እንኳን 400 ወጣቶችን አግኝተናል ወደማቆያም አስገብተናል ብለዋል፡፡

በሲዳማ ፤ወላይታ ፤ጉራጊ፤ ስልጤ፤ሀዲያ፤ከንባታን የመሳሰሉ የክልሉ አከባቢዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው በክልሉ የሚሰራባቸው ስፍራዎች ናቸው ተብሏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.