ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ ብቻ 3 ሺህ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው መግባታቸው ተገለጸ፡፡

የጋምቤላ ክልል መንግስት እንዳስታወቀው ባለፈው ሳምንት ብቻ ወደ ክልሉ 3 ሺ የሚሆኑ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በህገ ወጥ መንገድ ወደ ክልሉ መግባታቸውን አስታውቋል፡፡

ምንም እንኳን በክልሉ የሚገኙ ሁሉም የድንበር መውጫ መግቢያ በሮች ዝግ የተደረጉ ቢሆኑም ተጋክ በሚባለው ድንበር ላይ በ ህገወጥ መንገድ የገቡ ከ 3 ሺ በላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መኖራቸውን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ም/ሃላፊ ኦቶ ኦቶው ኦኮት ለ ኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ስደተኞቹን እዛው ድንበር አቅራቢያ ላይ በሚገኝ መጠለያ እንዲቆዩ መደረጉንም ከክልሉ ሰምተናል፡፡

ስደተኞቹ ባሉበት መጠለያ ሆነው የኮሮና ቫይረስ ህክምና ምርመራ እየተደረገላቸው መሆኑን የነገሩን አቶ ኦቶው እስካሁን ከ 100 በላይ ለሚሆኑ ስደተኞች ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን ነግረውናል፡፡

የስደተኞቹን የቀጣይ ሁኔታና መደረግ ስላለባቸው የቁጥጥር ተግባራት ከ ስደተኞችና ስደት ተመላሾች ኤጀንሲ ጋር እየተነጋገሩ መሆኑንም ተናግረዋል።

አሁንም ቢሆን ወደ ክልሉ በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው የሚገቡ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ለመቆጣጠር በየድንበር ላይ ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገ ይገኛል ብለውናል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በየውልሰው ገዝሙ
ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *