ቻይናዊያን የኢትዮ- ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ሾፌሮች ኮሮናን በመፍራት ስራቸውን እያቆሙ እንደሆነ ተገለጸ።

በኮሮና ቫይረስ ተይዘው የነበሩ አምስት የኢትዮ- ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር ሾፌሮች ማገገማቸው ተገልጿል፡፡

በሁለት ሀገራት ስምምነት የተቋቋመው የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር ትራንሰፖርት አክስዮን ማህበር በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የስራ መቀዛቀዝ እንደገጠመው ተገልጿል፡፡

የኢትዮ ጅቡቲ የባበር ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጥላሁን ሳርካ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በጅቡቲ የቫይረሱ ስርጭት የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱን ተከትሎ ምርቶችን ለማጓጓዝ ፈታኝ እንደሆነባቸው ተናግረዋል፡፡

አብዛኞቹ የባቡር ሾፌሮች የቻይና ዜጎች በመሆናቸው ቫይረሱን በመፍራት ስራቸውን በአግባቡ እየተወጡ እንዳልሆነም ተናግረዋል፡፡

ቀድሞውኑ የእውቀት ሽግግር በፍጥነት ባለመከናወኑ በሰለጠነ የሰው ሃይል ችግር ምክንያት ገቢያችንን በእጅጉ እየተቀዛቀዘብን ነው ብለዋል።

ከቻይናውያኑ ጋር አብረው ለሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን በሚገባ የእውቀት ሽግግር እየተፈጠረ አይደለም ያሉት ኢንጅነር ጥላሁን ይህ መሆኑ በፈለግነው ልክ የባቡሩን እንቅስቃሴ እያስኬድን አይደለም ብለዋል።

በኮሮና ቫይረስ ተይዘው የነበሩ አምስት የኢትዮ- ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር ሰራተኞች ማገገማቸውን ኢንጅነር ጥላሁን ተናግረዋል፡፡

በቫይረሱ ተይዘው የነበሩት እነዚህ ሰራተኞች ከአምስቱ አራቱ ቻይናዊያን የባቡር ሾፌሮች ሲሆኑ አንዱ በጅቡቲ በኩል የአክስዮን ማህበሩ ሰራተኛ ናቸው።

አምስቱ ሰራተኞች በተደረገላቸው የህክምና ክትትል ከቫይረሱ ማገገማቸውን ገልጸዋል።

ከነዚህ ሰዎች ጋር አካላዊ ንክኪ ነበራቸው የተባሉ 35 አሸከርካሪዎችም በለይቶ ማቆያ እንዲቁዩ ተደርጎ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው ነጻ መሆናቸው መረጋገጡንም ኢንጅነር ጥላሁን ተናግረዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *