ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,141 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃምሳ (150) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡
በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሰላሳ ስድስት (1636) ደርሷል፡፡
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አራት (4) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን ይህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ሁለት መቶ ሃምሳ (250) ደርሷል።
እንዲሁም በቫይረሱ ተይዞ የነበረና ተጓዳኝ ህመም የነበረበት የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ ህይወት ያለፈ ሲሆን ይህም ህይወታቸው ያለፈ ሰዎችን ቁጥር አስራ ስምንት (18) አድርሶታል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም











