ቤይንዝ በኤቨርተን የአንድ ዓመት ኮንትራት ማራዘሚያ ቀረበለት::

ኤቨርተን ለግራ መስመር ተከላካዩ ያቀረበው የአንድ ዓመት የኮንትራት ማራዘሚያ ነው። የ 35 ዓመቱ ተጫዋች ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በ30 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል። በ2007 በስድስት ሚሊየን ፓውንድ ዊጋንን ለቅቆ የሜርሲሳይዱን ክለብ ከተቀላቀለ ወዲህ በሰማያዊዎች ቤት ቆይቷል።

አዲሱ ስምምነት ቤይንዝ የተጫዋችነት ዘመኑን 417 ጊዜ ተሰልፎ በተጫወተበት ክለብ የሚያጠናቅቅበት ዕድል ይፈጥርለታል ። ምንም እንኳን ቤይንዝ በአዲሱ አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲ ስር ተሰልፎ መጫወት የቻለው በሶስት ጨዋታዎች ላይ ቢሆንም ጣሊያናዊው ከሜዳ ውጪ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ አሞካሽተዋል።

ባለፈው መጋቢት ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር 1ለ1 ከተለያዩበት ጨዋታ በኋላ አንቼሎቲ “እርሱን በቀጣዩ የውድድር ዘመንም ማቆየት ይጠበቅብናል” ብለዋል። “በልምምድ ሜዳ እና ሜዳ ላይ የሚያሳየው ተነሳሽነት አስገራሚ ነው። እጅግ ጠቃሚ ተጫዋች ነው። አሁንም ድረስ ጥሩ ተጫዋች ነው። በስኳዱ ውስጥ የካበተ ልምድ እና ጥሩ ስብዕና ካላቸው ተጫዋቾች አንዱ ነው።

በዚህ የውድድር ዘመን ሉካስ ዲኜ የመጀመሪያ ተመራጭ የግራ መስመር ተከላካይ በመሆኑ ቤይንዝ የመሰለፍ ዕድል ያገኘው በስድስት ጨዋታዎች ላይ ነው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *