ኢትዮጵያ ግብጽ እና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የገቡበትን ልዩነት በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት እንዲፈቱ ሩሲያ አሳሰበች።

ሩሲያ በአዲስ አበባ በሚገኘው ኢምባሲዋ በኩል ባወጣችው መግለጫ ኢትዮጵያ ግብጽ እና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የገቡበትን ልዩነት ዓለም አቀፍ ህጎችን እና እንደ ጎርጎሮሲያውያን ዘመን አቆጣጠር በ2015 ካርቱም ላይ በተፈራረሙት ስምምነት መሰረት እንዲፈቱ ምክረ ሃሳቧን ለግሳለች።

ሩሲያ እንዳለችው የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ ከ2 ሳምነት በፊት ሶስቱ አገራት በግድቡ ዙሪያ ያላቸውን ልዩነት እንዲፈቱ በሚል ያስቀመጡትን የመፍትሔ አማራጭ እንደምትደግፍም አስታውቃለች።

የህዳሴውን ግድብ ጉዳይ በአንክሮ እንደምትከታተለው የገለጸችው ሩሲያ የናይል ወንዝ ተፋሰስ አገራት ውሃውን ለጋራ ጥቅም እና በትብብር እንዲያውሉትም አስታውቃለች።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሳሙኤል አባተ
ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *