ካሊፋ ሃፍታር የትሪፖሊ አውሮፕላን ማረፊያን ከመነጠቃቸው ከሰዓታት በፊት በግብጽ ጉብኝት ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው በተባበሩት መንግስታት እውቅና ያለው የሊቢያ መንግስት ትሪፖሊ አየር ማረፊያን ከሃፍታር ጦር መንጠቁን ከማስታወቁ ከሰዓታት በፊት ፤መሰረቱን በሊቢያ ምስራቃዊ ክፍል ያደረገውና ራሱን የሊቢያ ብሄራዊ ጦር ብሎ የሚጠራው ቡድን መሪ ጄኔራል ካሊፍ ሃፍታር ግብጽን መጎብኘታቸው ተሰምቷል፡፡

በቆይታቸውም ከግብጹ ምክትል መከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል ነው የተባለው፡፡

ሃፍታር በግብጽ፣ ሩሲያና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሚደገፍ ሲሆን አለም አቀፍ እውቅና ያለው የሃገሪቷ መንግስት ደግሞ በኳታርና ቱርክ ይደገፋል፡፡

ሁለቱ ተቀናቃኞች እርስ በርሳቸው ሲፋለሙ የቆዩ ሲሆን ረቡእ እለት ትሪፖሊን ሙሉ በሙሉ ከሃፍታር ጦር ነጻ ማድረጉን የሃገሪቷ መንግስት አስታውቋል፡፡

ከ9 ዓመት በፊት የመሀመድ ጋዳፊ አምባገነናዊ ስርዓት አንግሸገሸን ዲሞክራሲ እንፈልጋለን በሚል ወደ አደባባይ የወጡት ሊቢያውያን አሁን ላይ በሰላም ወጥተው መግባት ናፍቋቸዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *