“አሁን ላይ ብቸኛው በሽታ ዘረኝነት ነው” ስቴርሊንግ

የእንግሊዝ እና ማንቸስተር ሲቲው የፊት መስመር ተሰላፊ ራሂም ስቴርሊንግ በእንግሊዝ እየተደረጉ ያሉ የተቃውሞ ሰልፎችን ደግፏል። “በአሁኑ ወቅት እየተዋጋነው ያለነው ብቸኛ በሽታ ዘረኝነት ነው” ብሏል። በእንግሊዝ እየተከናወነ ባለው Black Lives Matter የሚል መርህ ባላቸው ሰልፎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተሳትፈዋል።

የእንግሊዝ መንግስት ግን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሰዎች ባይሰበሰቡ መልካም ነው በማለት እያስጠነቀቀ ይገኛል ። “በአሁኑ ወቅት እጅግ አስፈላጊው ነገር ይሄው ነው ። ያለ ከልካይ ለዓመታት ሲፈጸም የነበረ በደል ነው ” ብሏል የ25 ዓመቱ ስቴርሊንግ። ። የአሜሪካዊውን ጆርጅ ፍሎይድ ሞት ተከትሎ በለንደን፣ ብሪስቶል፣ ማንቸስተር፣ ዎልቨርሃምፕተን ፣ ኖቲንግሃም ፣ ግላስኮው እና ኤደንብራ የተቃውሞ ሰልፎች ተከናውነዋል። የ46 ዓመቱ ፍሎይድ በግንቦት 25 በፖሊስ እጅ አደባባይ ላይ መንገደኞች ለህይወቱ እየለመኑ መገደሉ ይታወቃል።

ድርጊቱ ከተፈጸመ እና ተቃውሞ ከተቀሰቀሰ በኋላ በድርጊቱ ተሳታፊ የነበሩ አራቱ ፖሊሶች ክስ ተመስርቶባቸዋል። ስቴርሊንግ ከቢቢሲ ኒውስ ናይት ጋር ባደረገው ቆይታ “እንደወረርሽኙ ሁሉ ለዘረኝነትም መፍትሄ ማበጀት ይኖርብናል” ብሏል። “ሰዎችን እስካላጠቁ እና የሰዎችንሰየቁች እስካልሰባበሩ እንደዚሁም ሰላማዊ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ እስከፈጸሙት ድረስ ልንደግፋቸው ይገባል ” ብሏል።

በመጪው ሰኔ 17 ከሲቲ ጋር ወደ ፕሪምየር ሊግ ውድድር የሚመለሰው ስቴርሊንግ ከዚህ ቀደም እርሱ ላይ ስለተሰነዘሩ የዘረኝነት ጥቃቶች እና ሚዲያው ጥቁር ተጫዋቾችን የሚስልበት መንገድ ልክ አይደለም ብሎ አስተያየት መስጠቱ ይታወቃል። እንደዚህ አደባባይ ወጥቶ ድምጹን ማሰማቱ እንደ እግር ኳስ ተጫዋች ስራውን ያከብድበት እንደሆን ሲጠየቅ ” የመጀመሪያው እና ቀዳሚው ነገር እንደዚህ ያለው ነገር ዓይኔ ስር እየተፈጸመ ስለ ስራዬ ላስብ አልችልም።

የማስበው ትክክል ድለሆነው ነገር ብቻ ነው ። “በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት ሲፈጸም የነበረ በደል ነው። ሰዎች ታክቷቸዋል። ለለውጥ ተዘጋጅተዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *