የደቡብ አሜሪካ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከቁጥጥራቸዉ ዉጭ እየሆነባቸዉ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ሲኤን ኤን እንዳለዉ የቫይረሱ ስርጭት በአሁኑ ወቅት ከሁሉም የዓለማችን ክፍል በደቡብ አሜሪካ ሀገራት ያለዉ ሁኔታ የከፋ ነዉ፡፡

በቀጠናዉ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በሮና ቫይረስ ሲያዙ 60 ሽህ የሚሆኑት ደግሞ በቫይረሱ ህይወታቸዉ አጥተዋል፤አሁንም ቢሆን የቫይረሱ ስርጭት የመቀነስ አዛማሚያ አለማሳየቱም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ከነዚህ ሀገራት መካከል በብራዚል ብቻ 646 ሽህ የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ከ35 ሽህ በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

በሃገሪቱ የተጠቂዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ በመምጣቱ ሰዎች ላይ የተሰጠረዉን ጭንቀት ለመቀነስ በሚል የሟቾችና የተጠቂዎች ቁጥር በመንግስት መስሪያ ቤቶች ድረ-ገጾች ላይ ይፋ እንዳይደረግ ተከልክሎም ነበር፡፡

በሜክሲኮ ከ110 ሽህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከ13 ሽህ በላይ የሚሆኑት ለሞት ተዳርገዋል፡፡ በፔሩም 188 ሽህ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን በኡራጓይም 830 የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለዉ በቀጠናዉ ያለዉ የቫይረሱ ስርጭት አስደንጋጭ የሚሆነዉ በየእለቱ ከመቀነስ ይልቅ በፍጥነት እየጨመረ በመሄዱ መሆኑን ይገልጣል፡፡

ሀገራቱ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ሆነዉ ደግሞ የእንቅስቃሴ ገደቦችን በማንሳት ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እንገባለን በሚል እየተቻኮሉ መሆኑ ከፍተኛ የህይወት ዋጋ እንዳያስከፍል ስጋት አለኝ ሲልም ድርጅቱ አሳስቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *