ምርጫው እንዲራዘም ከማይፈልጉት ፓርቲዎች ውስጥ ብልጽግና ቀዳሚ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አሕመድ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ሰተዋል፡፡

ዶ/ር አብይ አህመድ እንዳሉት ብልጽግና ፖርቲ ለምርጫው ከፍተኛ ዝግጅት ሲያርግ እንደነበረ አስታውሰዋል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ምርጫ ቦርድ ከስራው አስቸጋሪ ስለሚሆን ምርጫውን ማድረግ እንደማይችል ሲናገር እንደማይቀበሉት በወቅቱ ለምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ጋር ሀይል በተቀላቀለበት ቃላት መመላለሳቸውን ተናግረዋል፡፡

ምርጫው በምንም መልኩ እንደማይቀየር ሳስረዳቸው እንዲያ ከሆነ እና መንግስት በስራዬ ጣልቃ ለመግባት ከሞከረ ስራዬን በፍቃዴ እለቃለሁ ማለታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተናግረዋል፡፡

ኃላ ላይም ከምክር ቤቱ አፈጉባኤ ጋር በመነጋገር ነገሩን መቀበላቸውን አስታውሰዋል፡፡

በተቃዋሚ ፖርቲዎች እየቀረበ ያለው ወቀሳ ተቀባይነት እንደሌለው የሚናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምስት ቢሊየን ችግኝ መትከል ከተቻለ ምርጫው መቅረቱ አግባብ እንደሌለው ለማስረዳት መሞከሩን ተናግረው ይህ ግን የተለየ መሆኑን ያስረዳሉ።

ችግኙን በተለያዩ ጊዜያትና የሰው መጠን ማስኬድ ይቻላል ምርጫ ግን እንደዚያ አይደለም ብለዋል፡፡

ይልቅ አሁንም እኚህ ፖርቲዎች ወገባቸውን ጠበቅ ቢያደርጉ ይሻላል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *