ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በ2012 በጀት ዓመት አስር ወራት ከወጪ ንግድ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል።

ይህ አፈፃፀም በ2011 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ከተገኘው 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር በ271 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ አለው።

በበጀት ዓመቱ አስር ወራት ከተያዘላቸው ዕቅድ በላይ አፈጻጸም ያስመዘገቡት አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ጫት ምርቶች ናቸው።

ከ50% እስከ 99% ክንውን ያስመዘገቡ ምርቶች እንደቅደም ተከተላቸው ቡና፣ የቅባት እህሎች፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ የጥራጥሬ ሰብሎች፣ ስጋ፣ ቅመማ ቅመም እና ወርቅ ናቸውተብሏል።

በሌላ በኩል ከተያዘው ዕቅድ አንጻር በውጭ ምንዛሪ ገቢ ከ50 በመቶ በታች ዝቅተኛ ገቢ ያስመዘገቡ የወጪ ንግድ ምርቶች ቆዳና የቆዳ ውጤቶች እና የቁም እንሰሳት መሆናቸው ሚኒስቴሩ ገልጿል።

አጠቃላይ የወጪ ንግድ ምርቶች ከአምናው ተመሳሳይ በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በገቢ ቡና 16%፣ አበባ 94%፣ የቅባት እህሎች 10% ፣ጫት 7%፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት 22%፣ ወርቅ 144 %፣ የቁም እንሰሳት 22% እና አትክልትና ፍራፍሬ 46% ጭማሪ ማሳየታቸው ተገልጿል።

በዋናነት የወጪ ንግድ ጭማሪ ያሣየበት ምክንያት የምርት ትንተናና የክምችት ክትትል በማድረግ በተገባው የኮንትራት ውል መሰረት እንዲላክ ድጋፍ ማድረግ፣ በህገ- ወጥ መንገድ በክምችት የተያዙ ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ ምርት ገበያ እንዲገቡ መደረጉ ዋነኞቹ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል።

እንዲሁም በተወሰኑ ከተሞች ከፍተኛ ህገ- ወጥ የምርት ክምችት መኖሩን በድንገተኛ ቆጠራና ክትትል በማድረግ ህጋዊ እርምጃ በመወሰዱ ለተገኘው ገቢ መጨመር ተጨማሪ መክንያቶች ናቸው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *