ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ እንደምታቋርጥ አስታወቀች።

ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያላትን ማንኛውንም አይነት የግንኙነት መስመር እንደምታቋርጥ ነው ያታወቀችው፡፡

ይህ የግንኙነት መቋረጥም በመሪዎቹ መካከል ያለውንም ግንኙነት እንደሚጨምር ነው የተነገረው፡፡

ሰሜን ኮሪያ ይህ ውሳኔ ደቡብ ኮሪያ ጠላታችን ስለመሆኗ በግልፅ የምናሳውቅበት እርምጃ ነው ብላለች፡፡

በሰሜን ኮሪያ ድንበር ላይ በምትገኘው ኬዚዮን ከተማ በሀገራቱ መካከል ያሉ የስልክ ግንኙነቶች የሚስተናገዱበት ማዕከልም ከዛሬ ጀምሮ የስልክ ጥሪዎችን ማስተናገድ ያቆማል ነው የተባለው።

ሁለቱ ሀገራት ከረጅም ጊዜ ፀብ በኋላ በአውሮፓያኑ 2018 ነበር ይህን የሚያገናኘቸውን ፅህፈት ቤት ያቋቋሙት።

ሰሜን ኮሪያ ከደበብ ኮሪያ ጋር ያገናኛት የነበረው የኸው ቢሮ በከሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዝግ ሀኖ በቆየበት ወቅት ሀገራቱ በስልክ ይገናኙ የነበር ቢሆንም አሁን ግን ከናካቴው የግንኙነት መስመሮቻው ሁሉ እንደሚቋረጥ ሰሜን ኮሪያ ማስታወቋን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *