ኢትዮጵያ በሚያዚያ ወር ወጪ ንግድ 329 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ።

የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ እንዳመለከተው በ2012 በጀት ዓመት በሚያዚያ ወር ከግብርና ፣ ከማኑፋክቸሪንግ ፣ ከማዕድን ምርቶች ዘርፍ እና ከሌሎች ምርቶች 365.1 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ነበር።

አፈጻጸሙም 329 ነጥብ 3 ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን የእቅዱን 90 በመቶ መሳካቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ይህ አፈፃፀም ከአምናው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወር ከተገኘው 249 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ጋር ሲነጻጸር በ79 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በሚያዚያ ወር አገሪቷ ከግብርናው ዘርፍ 237.47 ሚሊዮን ዶላር፣ ከማኑፋክቸሪንግ 23.18 ሚሊዮን ዶላር፣ ከማዕድን ዘርፍ 64.50 እና ከሌሎች ምርቶች 4.14 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች፡፡

ከተያዘላቸው ዕቅድ በላይ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ዋና ዋና የወጪ ንግድ ምርቶች ወርቅ፣ አበባ እና ቡና ናቸው፡፡

የዕቅዱን ከ50% እስከ 99% ክንውን ያስመዘገቡ ምርቶች ደግሞ የቅባት እህሎች፣ የጥራጥሬ ሰብሎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ስጋ እና ጫት ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ለወሩ ከተያዘው ዕቅድ አንጻር በውጭ ምንዛሪ ገቢ ከ50 በመቶ በታች ዝቅተኛ ክንውን ያስመዘገቡ የወጪ ንግድ ምርቶች እንደቅደም ተከተላቸው ቅመማ ቅመም፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ የቁም እንስሳት እና ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ናቸው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *