በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን አለፈ።

ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ እንዳስታወቀው በአሜሪካ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር በአሁኑ ወቅት ከ2 ሚሊዮን በላይ ሆኗል።

ይህም አሃዝ በዓለም ቀዳሚዋ ሲደርጋት በሁለተኝነት ከምትከተላት ከብራዚል በሦስት እጥፍ የበለጠ ነው ተብሏል።

በብራዚል በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ772,400 በላይ ነው።

አሜሪካ ከየትኛውም አገር በላይ በርካታ ቁጥር ያለውን ምርመራ የምታደርግ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ በየቀኑም እስከ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ናሙናዎችን ትመረምራለች።

ይህም በበሽታው የተያዙ በርካታ ሰዎች እንዲገኙ ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ እንደሆነ ይነገራል።

በአሜሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኮቪድ-19 ምርመራ ስለሚደረግ በየዕለቱ ከሚደረገው 500 ሺህ የሚጠጋ ምርመራ ውስጥ 20 ሺህ የሚደርሱ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ይገኛሉ።

በበሽታው በሚያዙ ሰዎች ቁጥር ብቻ ሳይሆን አሜሪካ በሚሞቱ ሰዎች ብዛትም ቀዳሚ ናት።

እስካሁንም በአገሪቱ 112 ሺህ 878 ሰዎች በወረርሽኙ ሰበብ ህይወታቸውን አጥተዋል።

ይህም በጣም ከፍተኛ ቁጥር ሲሆን በሁለተኝነት የምትከተላት ዩናይትድ ኪንግደም የሞቱባት ሰዎች 41 ሺህ 213 ሲሆን ሦስተኛዋ ብራዚል ደግሞ 39 ሺህ 680 ዜጎቿን አጥታለች።

በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 4 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *