በኢትዮጵያ ተጨማሪ 245 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,709 የላብራቶሪ ምርመራ 245 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2,915 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 172 ወንድ እና 73 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 85 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 241 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አራቱ (4) የውጭ ሀገር ዜጋ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 190 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 17 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 16 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 15 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 4 ሰዎች ከደቡብ ክልል እንዲሁም 3 ሰው ከአማራ ክልል ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት አስራ ሰባት (17) ሰዎች (16 ከአዲስ አበባና 1 ከደቡብ ክልል ትላንት በክልሉ ሪፖርት የተደረገ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 451 ደርሷል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያን
ሰኔ 5 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *