ቡሩንዲ ከነገ በስትያ አዲሱን ፕሬዝዳንቷን ትሾማለች።

የብሩንዲ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እንደገለፀው አዲስ የተመረጡት ፕሬዝዳንት ኤቫሪስቴ ንዳዪሽምዬ ከታቀደው 2 ወራት ቀደም ብለው ከነገ በስትያ ሀገሪቷን በፕሬዝዳንትነት ለማገልገል ቃለ መሀላ ይፈፅማሉ፡፡

በአለ ሲመቱ ከታቀደው በሁለት ወራት እንዲፈጠን የተደረገው በስልጣን ላይ የነበሩት ፔሬ ንኩሩንዚዛ ባለፈው ሳምንት ህይወታቸው በማለፉ ነው፡፡የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለዲፕሎማቶችና ለውጪ ሀገር ድርጅቶች በአለ ሲመቱን እንዲካፈሉ ደብዳቤ ፅፈዋል፡፡

እንደ ንኩሪንዚዛ ሁሉ ኤቫሪስቴ ንዳዪሽምዬ የቀድሞ የሁቱ አማፂ ጦር ጀነራል ነበሩ፡፡በግንቦት ምርጫውን ከማሸነፋቸው በፊትም የንኩሪንዚዛን ድጋፍ ያገኙ ነበር።

በነሐሴ ቃለ መሐላ ሊፈፅሙ የነበረ ቢሆንም ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤቱ በፕሬዝዳንቱ ሞት ምክንያት 2 ወር ቀደም ሊያደርገው ችሏል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት

ሰኔ 9 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *