ኮሮናን ድል ነስቻለሁ በሚል አውጃ የነበረችው ኒውዚላድ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ አገኘች፡፡

ሀገሪቱ ምንም አይነት የኮሮና ቫይረስ ታማሚ አለመኖሩን ካወጀች ከ24 ቀናት በኋላ 2 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎችን ማግኘቷን አስታውቃለች፡፡2ቱም የቫይረሱ ተጠቂዎች ከእንግሊዝ ወደ ኒውዚላንድ ያቀኑ ሲሆን የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ለመታደም በልዩ ፍቃድ ወደ ሀገሪቱ የገቡ ናቸው ተብሏል፡፡

ባለፈው ሳምንት ኒውዚላንድ አገሪቱ ከቫይረሱ ነፃ የሆነች መሆኗን በመግለፅ ሁሉንም የአገር ውስጥ ገደቦችን አንስታ ነበር ፡፡ሆኖም ግን ፣ ጥብቅ የድንበር ገደቦች በቦታው መኖራቸውን ቀጥለዋል – ዜጎች እና አስፈላጊ ሠራተኞች ብቻ ተፈቅዶላቸዋል ፡፡

በኒውዚላንድ የመጡ ሁሉም ሰዎች ኮቪድ -19 ምርመራ ይደረግባቸዋል እናም ለ 14 ቀናት ብቸኛ ወይም ገለልተኛ ሆነው ማለፍ አለባቸው።

በሀገሪቱ ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ ከተገኘባቸው አዲስ 2 ሰዎች ጋር ተደምሮ በአጠቃላይ 1ሺ 506 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ የሟቾች ቁጥርም 22 መሆኑን ቢቢዚ ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም

ሰኔ 9 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *