በኢትዮጵያ ተጨማሪ 195 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ ተጨማሪ የሁለት ሰው ህይወት ማለፉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,853 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ዘጠና አምስት (195) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡
በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ አራት (3,954) ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰማንያ አምስት (85) ሰዎች (73 ከአዲስ አበባ እና 5 ከኦሮሚያ ክልል፣ 5 ከአማራ ክልል እና 2 ከትግራይ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን ይህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠኝ መቶ ሰላሳ አራት (934) ደርሷል።

እንዲሁም ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ የሁለት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ይህም ህይወታቸው ያለፈ ሰዎችን ቁጥር ስልሳ አምስት (65) አድርሶታል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/ethiofm107dot8

የዩቲዩብ ገጻችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቪድዮቻችንን ይመልከቱ::
https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA…

ሰኔ 11 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *