በዓለማችን በይፋ ከተነገረዉ ዉጭ በትንሹ ከ130 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን አጥተዋል ተባለ፡፡

በ27 ሀገራት ላይ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት፣በጥናቱ በተካተቱ በሁሉም ሀገራት የሞት መጠን በአስደንጋጭ ሁኔታ ጨምሮ ተገኝቷል፡፡

በቢቢሲ የተሰራዉ ይህ ጥናት፣ በኮሮና ቫይረስ ሞቱ የተባሉትን ሰዎች ሳያካትት የተሰራ ሲሆን፣በዚህም በመንግስታት ሪፖርት ያልተደረጉና ለሞታቸዉ ምክንያት ግን የኮሮና ቫይረስ ሊሆን እንደሚችል ምልክት ያሳዩ ከ130 ሽህ በላይ ሰዎች መሞታቸዉን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

በጤናዉ ዘርፍ ላይ የኮሮና ቫይረስ ባደረሰዉ ተጽዕኖ በሌሎች በሽታዎች የተጠቁና ህክምና ሳያገኙ የሞቱ በርካታ ሰዎች መኖራቸዉንም ተገንዝቤያለሁ ብሏል ጥናቱ፡፡

ለሞት የተዳረጉት ከ130 ሽህ በላይ ሰዎች ምርመራ ያልተደረገላቸዉና ከሆስፒታል ዉጭ የሞቱ ሲሆን ብራዚል፣ጣሊያን፣እንግሊዝና ደቡብ አፍሪካ በብዛት ይህ አሳዛኝ ድርጊት የተስተዋለባቸዉ ሀገራት ናቸዉ ተብሏል፡፡

ለማሳያነትም በዩናይትድ ኪንግደም በጠቅላላዉ 64 ሽህ 500 ሰዎች ለሞት የተዳረጉ ሲሆን ሪፖርት የተደረገዉ ግን 42 ሽህ 153 ብቻ ነዉ፤ይህም ከ22 ሽህ በላይ ሰዎችን ያላጠቃለለ ሪፖርት ነዉ ተብሏል፡፡

በጣሊያንም 42 ሽህ 900 ሰዎች መሞታቸዉ ሲረጋገጥ የተነገረዉ ግን 34 ሽህ 448 ሰዎች መሞታቸዉ መሆኑን ይገልጣል፡፡

ጥናቱ እንደሚለዉ አሁንም ቢሆን በተለያዩ ሀገራት ምርመራ ሳያደርጉና የሆስፒታል በር ሳያዩ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ለቀጣይ በርከት ላሉ ወራት የሚቀጥል መሆኑን የሚጠቁም ነዉ፡፡

እናም ሀገራት የምርመራ አቅማቸዉን ማሳደግና ለብዙሃኑ ተደራሽ ማድረግ ካልቻሉ፣በቫይረሱ ምክንያት በየቤታቸዉ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ ሊያሻቅብ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡

እስከዚህ ሰዓት ድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ከ 448 ሽህ በላይ የደረሰ ሲሆን ከ 8 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ በቫይረሱ መጠቃታቸዉን የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ያስረዳል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

የዩቲዩብ ገጻችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቪድዮቻችንን ይመልከቱ::

https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA?sub_confirmation=1

በሙሉቀን አሰፋ
ሰኔ 11 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *