የደቡብ ክልል ምክር ቤት የሲዳማ ዞን የአገሪቱ 10ኛ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ የሥልጣን ርክክብ ለማድረግ የቀረበውን አጀንዳ ተቀብሎ አጸደቀ።

ምክር ቤቱ አጀንዳውን ያጸደቀው ከደቂቃዎች በፊት በሀዋሳ ከተማ በጀመረው የምክር ቤቱ አምስተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት ሁለተኛ አስቸኳይ ጉባኤው ነው ።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የምክር ቤቱን የመወያያ አጀንዳዎች ያቀረቡት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሄለን ደበበ ምክር ቤቱ በዚህ ጉባኤ ከሚመለከታቸው አጀንዳዎቹ መካከል አንዱ የሲዳማ ዞን የሥልጣን ርክክብ መሆኑን ለጉባኤው አባላት ገልጸዋል።

አሁን ለጉባኤው የቀረበው አጀንዳ የሲዳማ ህዝብ በራስ ገዝ አስተዳደር ( ክልል ) ለመደራጀት ባለፈው የኅዳር ወር ያካሄደውን ሕዝበ ውሳኔ ተከትሎ የክልል ምስረታው ሂደት ተጓቷል በሚል ከተለያዩ አካላት እየቀረበ ለሚገኘው ወቀሳ የመጨረሻ አልባት ይሰጣል ተብሎ ታምኖበታል።

ጉባኤው በተጨማሪም በክልሉ የኮቪድ 19 ወርረሽኝን ለመከላከል የተከናወኑ ሥራዎችን የሚገመግም ሲሆን ለክልሉ የ2012 ዓም ተጨማሪ በጀትም ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ ሕዝባችን በክልል ለመደራጀት ላቀረበው ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ አልሰጠም በሚል ራሳቸውን ከአባልነት ማግለላቸውን ከቀናት በፊት ያስታወቁት 38 የወላይታ ሕዝብ ተወካዮች በዚህ ጉባኤው አልተገኙም።

ጉባኤው የአሁኑ ጉባኤ እየተካሄደ የሚገኘው ከውትሮው በተለየ ሁኔታ በከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ ውስጥ ሆኖ ነው ።

ቀደም ባሉት ጊዜያት ጉባኤው የሚመክርባቸው አጀንዳዎች ከቀናት በፊት ለአባላቱ ይደረሱ የነበረ ቢሆንም በዛሬ ጉባኤ ግን አጀንዳዎቹ የቀረቡት አባላቱ ወደ ጉባኤው አዳራሽ ገብተው ቦታቸውን መያዘቸው ከተረጋገጠ በኋላ ነው።

ጉባኤው በአሁኑ ሰዓት በክልሉ የኮቪድ 19 ወርርሽኝን ለመከላከል በተከናወኑ ሥራዎች ዙሪያ በክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ በአቶ አቅናው ካውዛ በቀረበውን ሪፖርት ላይ እየተዋያየ መሆኑን የጀርመን ድምጽ ሬድዮ DW ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

የዩቲዩብ ገጻችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቪድዮቻችንን ይመልከቱ::
https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA…

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 11 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *