የገቢዎች ሚኒስቴር አምስተኛ የግብር መክፈያ ቅርንጫፍን በአዲስ አበባ ሊከፍት መሆኑን አስታወቀ።

በአዲስ አበባ የሚገኙ 24 ሺህ 900 የፌደራል ግብር ከፋዮችን እንደ አዲስ በአምስት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ይደራጃሉ ተብሏል፡፡

በአራት ቅርንጫፎቹ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሀምሌ 1 ጀምሮ አምስተኛውን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሊከፍት መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ቀደም ሲል ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ የምስራቅና ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እንዲሁም የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል ነበር የተደራጀው፡፡

በዚህም መሰረት ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የነበሩት 700 ግብር ከፋዮች ወደ 623 ዝቅ ብሎ ኮንስትራክሽን፣ማዕድን፣ ሁሉም ባንኮችና ኢንሹራንስ ድርጅቶቻቸውን፣ሁሉም የመንግስት የልማት ድርጅቶችና የባለበጀት መስሪያ ቤቶች (1 ቢሊዮንና ከዚያ በላይ ዊዝ ሆልድ የሚያደርጉት) አካቶ ተደራጅቷል፡፡

4400 ግብር ከፋዮች የነበሩት መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ደግሞ ወደ 3736 ዝቅ ብሎ የከፍተኛ ግብር ከፋይነትን መስፈርት ያላሟሉ የኮንስታረክሽንና የማዕድን ድርጅቶች ፣ ሁሉም የኢንሹራንስ ድርጅቶች(ኢንሹራንስ እንጅ ባንክ የሌላቸው)፣ከ1 ቢሊዮን በታች ዊዝ ሆልድ የሚያደርጉ ባለበጀት መስሪያ ቤቶችን ይዞ ተደራጅቷል፡፡

20 ሺህ 795 አነስተኛ ግብር ከፋዮች የነበራቸው የምስራቅና የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ድግሞ አንድ አዲስ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የገቢዎች ሚኒስቴር አምስተኛ የግብር መክፈያ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከሀምሌ 1 ጀምሮ እንደሚከፍት ገለፀተጨምሮ ከ6 ሺ አስከ 7 ሺ ሁነው ይደራጃሉ ተብሏል፡፡

ምደባው በግብር አስተዳደር አዋጁ ላይ የግብር ከፋዮችን ደረጃ በየሁለት አመቱ ማጥናትና ማደረጃት እንደሚያስፈልግ የተቀመጠውን ህግና አለም አቀፍ ተሞክሮን መነሻ በማድረግ የሚከናወን እንደሆነ ተገልፆአል፡፡

ምደባውን ለመስራትም የድርጅቱ አመታዊ ሽያጭ፣ለገቢ የነበረው አስተዋጽኦ፣የድርጅቱ ሀብት፣ያለፉት 3 አመታት የህግ ተገዥነት ታሪክ፣የተሰማራበት የንግድ ዘርፍና የባለቤትነት ሁኔታ (የመንግስት፣ የግል፣ በጎ አድራጎትና ኢንባዎች) በሚል መስፍርት መሰረት ድልድሉ እንደተካሄደ ተገልጻል፡፡

ምደባው የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ በማድረግ የግብር ከፋዮችን እርካታ ለመጨመር፣የህግ ተገዥነትን ወደ ተሸለ ደረጃ ለማድረስና የቴክኖሎጅ አጠቃቀምን ለማሰደግና ግብር ከፋዮችን በቅርበት ለመደገፍም ታስቦ የተሰራ መሆኑ ተገልጸዋል፡፡
ምደባው ከሀምሌ 1 ጀምሮ ተግበራዊ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

የዩቲዩብ ገጻችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቪድዮቻችንን ይመልከቱ::

https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA?sub_confirmation=1

በሔኖክ አስራት
ሰኔ 11 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.