ግብጽ የምታደርገዉን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ሉዓላዊነቴን ከመድፈር ለይቼ አላዉም ስትል ሊቢያ አስታወቀች፡፡

ግብጽ በምስራቃዊ ትሪፖሊ 450 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዉ ሰርጥ ከተማ ያለዉ እንቅስቃሴ ለደህንነቴ አስጊ ነዉ በሚል በአካባቢዉ ወታደር ልታሰማራ መሆኑን አስታዉቃለች፡፡

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ሃገሪቱን በስተ-ምዕራብ ከሊቢያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ የሚገኝ ሰራዊታቸዉን በጎበኙበት ወቅት ሰራዊቱ የግብጽን ደህንነት ለማስጠበቅ ለሀገር ዉስጥም ሆነ ዉጫዊ ተልዕኮ ዝግጁ እንዲሆን መናገራቸዉ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎ በሊቢያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እዉቅና ያለዉ መንግስት፣ የዉስጥ ጉዳያችን የእኛ የሊቢያዊያን ጉዳይ ብቻ ነዉ፤ የማንም ጣልቃ ገብነት አያስፈልገንም፤ከዚያ ዉጭ ግብጽ በቀጠናዉ የምታደርገዉን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ሉዓላዊነቴን ከመጣስ ለይቼ አላየዉም ብላለች፡፡

ግብጽ ስርጥና ጁፍራ ለኔ ቀይ መስመሮች ናቸዉ ማለቷ፣በቀጥታ በሉዓላዊነታችን ላይ ጣልቃ ለመግባት ያላትን ፍላጎት በግልጽ ያሳየ ነዉ፤ይህን ቀለል አድርጌ የምመለከተዉና በዝምታ የማልፈዉ ጉዳይ አይደለም ስትል ግብጽን እንዳስጠነቀቀች ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *