በስትሮክ ህመም ምክንያት ለሁለት ወራት ራሷን ስታ ሆስፒታል የነበረችው እንስት ስትነቃ አራት ቋንቋዎችን አቀላጥፋ መናገር መቻሏ ተሰማ፡፡

እንግሊዛዊቷ የ31 አመት እድሜ ያላት ግለሰብ በደረሰባት ህመም ምክንያት ለሁለት ወራት ያክል መናገር ተስኗት ነበር፡፡

ግለሰቧ ለሁለት ተከታታይ ሳምንታት ከባድ የሆነ እራስ ምታት የነበረባት ሲሆን በተደረገላት የህክምና ምርመራም ስትሮክ እንደያዛት ነው የተነገረው፡፡

አሁን ላይ በጥሩ ጤንነት ላይ ስትገኝ ከህመሟ ስትነቃ ከዚህ በፊት መናገር የማትችላቸው ቋንቋዎችን መናገር እንደቻለች አስገራሚ ወሬዎችን በማሰራጨት የሚታወቀው ኦዲቲ ሴንትራል የተሰኘው የወሬ ምንጭ ዘግቧል፡፡

በእንግሊዝ በስደተኞች ማእከል የምትገኝው ይህቺ ወጣት ከሩስያ ነበር በስደት ወደ እንግሊዝ ያቀናቸው፡፡

ወጣቷ ከህመሟ ስትነቃ ፈረንሳይኛ ጣሊያንኛ የሩስያ እና የፖላድ ቋንቋዎችን አቀላጥፋ መናገር ችላለች ተብሏል፡፡

ወጣቷ ከሶስት ሳምት የሆስፒታል ቆይታ በኃላ ወደ ቤቷ መመለሷ ተገልጿል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔበኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *