ዶናልድ ትራምፕ ለውጪ ሀገር ሰራተኞች የመኖሪያ ፍቃድም ሆነ ቪዛ የመስጠት ሂደት እንዲቆም መወሰናቸው ተነገረ፡፡

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም ለውጪ ሀገር ሰራተኞች ይሰጡት በነበሩ አንዳንድ የመኖሪያ ፍቃድ እንዲሁም ቪዛዎች ላይ እገዳ መጣላቸውን አስታውቀዋል፡፡

ይህ ለአፍታ እንዲቆም የተወሰነው የመኖሪያ ፍድም ሆነ ቪዛ የመስጠቱ ሂደት እስከ አውሮፓውያኑ 2020 ማገባደጃ ድረስ የሚዘልቅ ይሆናልም ብለዋል፡፡

ይህ ውሳኔም የሰለጠኑ የቴክኖሎጂ ሰራተኞች ፣ የትርፍ ሰዓት ሰራተኞች ፣ ከፍተኛ የሥራ አስፈፃሚዎች ላይ ተጽዕኖ እንደሚፈጥርም ተነግሯል፡፡

ከዋይ ሀውስ የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ይህ ለውጭ ሀገር ሰራተኞች ይሰጥ የነበረው የቪዛ ክልከላ በወረርሸኙ ምክንያት ኢኮኖሚያቸው ለተጎዳ አሜሪካውያን የስራ እድል ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡

ዋይት ሀውስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ከለላ በማድረግ የኢሚግሬሽን ህጎችን ለማፅናት እየተጠቀሙበት ነው ሲሉ በርካቶች ይህንን ውሳኔ እየተቹ መሆናቸውን በቢሲ ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *