ኢትዮጵያ ከጅቡቲ እና ሩዋንዳ ጋር በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን መለዋወጥ የሚያስችላትን ስምምነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልታጸድቅ ነው።

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

ምክር ቤቱ በነገው ውሎው ለማየት 15 አጀንዳዎችን ያዘጋጀ ሲሆን ከጅቡቲ እና ከሩዋንዳ ጋር በወንጀል የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎችን መለዋወጥ የሚያስችሉ ስምምነቶችን እንደሚያጸድቅ የጠበቃል።

ይህን ስምምነት ኢትዮጵያ ከነዚህ አገራት ጋር ከዚህ በፊት የተፈራረመች ሲሆን ይህ ስምምነት ከጸደቀ ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ወይም ከሩዋንዳ በወንጀል የምትፈልገው ሰው ቢኖር አገራቱ አሳልፈው ይሰጧታል።

አገራቱ ከኢትዮጵያ የሚፈልጉት ተፈላጊ ወንጀለኛ ካለም አሳልፋ የመስጠት ግዴታ ይኖርባታል ማለት ነው።

ይሁንና ይህ ስምምነት ወደ ተግባር የሚቀየረው ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአብላጫ ድምጽ ሲያጸድቀው ብቻ ይሆናል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ለአንበጣ መንጋ ለመከላከል እና የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚል ከተለያዩ ተቋማት የተበደረቻቸው የብድር ስምምነቶችነም እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

እንዲሁም የማዕድን ግብይት ረቂቅ አዋጅን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ እንደሚያጸድቅ እና ለዝርዝር እይታ ወደ ቋሚ ኮሚቴዎች እንደሚመራም ይጠበቃል ሲል የምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሳሙኤል አባተ
ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *