አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ (IMF) የዓለም ኢኮኖሚ ቀደም ሲል ከተገመተው የከፋ እንደሚሆን አስታወቀ።

በአንጻሩ ቻይና በዚህ አመት በአንድ በመቶ ኢኮኖሚዋ ሲያድግ፤በሚቀጥለው አመትም የ8.2 በመቶ እድገት ያስመዘግባል ብሏል፡፡

የአሜሪካ ኢኮኖሚ በዚህ አመት 8 በመቶ ይቀንሳል ፤ በሚቀጥለው አመት ደግሞ በ4.8 በመቶ መሻሻል ያሳያልም ተብሏል፡፡

አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም IMF ቀደም ሲል ለዚህ አመትና ለሚቀጥለው አመት አስቀምጦት የነበረው የዓለም አኮኖሚ እድገት ከተነበየው የከፋ እንደሚሆን ነው ባወጣው ሪፖርት ያመለከተው፡፡

ተቋሙ በያዝነው 2020 የአለም ኢኮኖሚ 5 በመቶ እንደሚቀነስ የተነበየ ቢሆንም ከ10 ሳምንታት በፊት በሚያዚያ ወር ከተነበየው በእጅጉ የከፋው ስለመሆኑ ቢቢሲ በቢዝነስ አምዱ ዘግቧል፡፡

የእንግሊዝ ኢኮኖሚ በተያዘው አመት ከ10 በመቶ በላይ እንደሚቀንስ ይጠበቃል፤ በበ2021 ግን በግማሽ መሻሻል ያሳያል ተብሉ መተንበዩ ተገልጿል፡፡

ይሆን እንጂ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራው ከፍተኛ ቢሆንም ጣሊያን ፣ ፈረንሳይ እና ስፔን ይገጥማቸዋል ተብሎ ከሚታሰበው ጋር ሲወዳዳር ግን የተሻለ ስለመሆኑም አትቷል፡፡

የተቋሙ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጅቫ ሚያዚያ ወር ላይ የእንግሊዝ ኢኮኖሚ 6.5 በመቶ እንዲሁም በአለም ደግሞ 3 በመቶ እንደሚቀነስ መተንበዩን በአዲሱ ትንበያቸው ላይ አስታውሰዋል፡፡

ጣሊያንና ስፔን በዚህ ዓመት ኢኮኖሚያቸው 12.8 በመቶ ይቀንሳል ፤ በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ 6.3 በመቶ ይጨምራል፡፡ሩሲያ በያዝነው አመት 6.6 በመቶ ኢኮኖሚያዋ ሲቀንስ በሚቀጥለው ዓመት በ4.1 በመቶ ይሻሻላል፡፡

ህንድ 4.5 በመቶ በዚህ ዓመት ሲቀንስ፤ በሚቀጥለው ዓመት 6 በመቶ ይሻሻላል፡፡

ብራዚል በዚህ ዓመት በ9.1 በመቶ ሲቀንስ፤በሚቀጥለው ዓመት በ3.6 በመቶ መሻሻል ያሳያል ተብሏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *