የአሜሪካ ግምጃ ቤት ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ በስህተት ለሞቱ ሰዎች መላኩ ተነገረ።

የአሜሪካ ግምጃ ቤት ከኮሮና ወረርሽኝ የአደጋ ጊዜ ፈንዱ ላይ ከ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን በላይ ዶላር በስህተት ለሞቱ ሰዎች መላኩን በሀገሪቱ መንግስት ተቆጣጣሪዎች መታወቁ ተነገሯል።

ግኝቱ በፌዴራል ለኮሮና ቫይረስ እርዳታ በተደረገ ቅኝት የተገኘ መሆኑም ተገልጿዋል።

ከመጋቢት ጀምሮ ኮንግረንሱ ወደ አሜሪካን ኢኮኖሚ 2 ነጥብ 6 ትሪሊየን እንዲገባ አድርጓል ።

ሆኖም ገንዘቡን ለማዳረስ የነበረው መዋከብ ለስህተቱ እንዲከሰት ማድረጉን ተቆጣጣሪዎች አስረድተዋል።

የመንግሥት ተጠያቂነት ቢሮ ሪፖርት የግምጃ ቤት ዲፓርትመንቱ የሞት መረጃዎችን ሳያጠራ ቼኮችን በመላኩ ተጠያቂ ይሆናል መባሉን CNN ዘግቧል።

ሪፖርቱ አሜሪካ ለ ወረርሽኙ ከምታወጣው ወጪ 26 በመቶውን የሚይዘውንና Paycheck Protection Program የተሰኘ ለአነስተኛ ቢዝነሶች በቅናሽ ወለድ ብድር የሚቀርብበት ፈንድ በማጭበርበርና ተያያዥ ጉዳዮች ትልቅ አደጋ ውስጥ መውደቁንም ተነግሯል ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በዳንኤል መላኩ
ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *