በአዲስ አበባ እድሜያቸው ከ10 ዓመት በታች የሆኑ ሁለት ህጻናትን አስገድዶ የደፈረው ተከሳሽ የ25 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት።

በአሰገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የ25 አመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት፡፡

ተከሳሽ ደስታ ገበየሁ የተባለ ግለሰብ ቀኑ ነሀሴ ወር 2011 ዓ.ም ዕድሜቸው ስምንት እና ዘጠኝ አመት የሆነ ሁለት ሴት ህፃናቶችን በተለያዩ ቀናቶች በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ክልል ውስጥ በሚገኝው ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመባቸው በመሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዐቃቂ ቃሊቲ ምድብ ፅ/ቤት የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 627(1) ተላልፎ በመገኘቱ አራት ክሶችን መስርቶበታል፡፡

ተከሳሹ ፍርድ ቤት ቀርቦ ክሱን ክዶ የተከራከረ ቢሆንም ዐቃቤ ህግ በተከሳሽ ላይ ማስረጃ አቅርቦ በማሰማቱ እንዲሁም ተከሳሽ የተከሰሰበትን ክስ ሊያስተባብል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን በአራቱም ክሶች ጥፋተኛ ነህ በማለት ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ60 አመት እንዲቀጣ የፈረደበት ቢሆንም የተከሰሰበት ድንጋጌ ጣሪያው 25 ዓመት በመሆኑ በ 25 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ መስጠቱን የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ያደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡

በተመሳሳይ ዜና በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ ከህፃንነቷ ጀምሮ ያሳደጋትን የ15 ዓመት የእንጀራ ልጁን የደፈረው ግለሰብ በ11 ዓመት ከ9 ወር ጽኑ እስራት እንደተቀጣ ኮማንደር አጸደ ወርዶፋ ጨምረ ውገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሴቶችና ህፃናት ወንጀል ጋር ተያይዞ ከመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ 19 የምርመራ መዝገቦች ቀርበው የተጣሩ ሲሆን በ8 መዝገቦች ላይ ክስ ተመስርቶ ለችሎት መቅረባቸውን የአቃቂ ቃሊቲ ምድብ ጽፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ሲሳይ ጎኣ የገለጹ ሲሆን ቀሪዎቹ መዝገቦች በምርመራና በመወሰን ሂደት ላይ እንደሆኑ ምክትል ኃላፊ አብራርተዋል፡፡

በመሆኑም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግና ድርጊቱ ተፈፅሞ ሲያገኝም በተቻለ ፍጥነት ለፓሊስ ማሳወቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *