የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ ከሁለት ሳምንት በኋላ ውሀ መሙላት እንደሚጀምር አስታወቀች።

የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ከደቂቆዎች በፊት ባወጣው መግለጫ የአፍሪካ ህብረት ባዘጋጀው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ግብጽ እና ሱዳን ትናንት ውይይት አካሂደዋል።

በመግለጫ እንደተጠቀሰው አገራቱ በግድቡ ሙሌት እና አስተዳደር ላይ የሚድረገው ድርድር በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት እንዲጠናቀቅ ተስማምተዋል።

ኢትዮጵያ በመጭዎቹ ሁለት ሳምንታት የግድቡን ቀሪ ግንባታ ስራዎች በማጠናቀቅ ግድቡ ውሀ መያዝ ይጀምራል ተብሏል።

በነዚህ ሁለት ሳምንታትም ሀገራቱ ከስምምነት ላይ ለመድረስ መወሰናቸውም ተገልጿል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 20 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *