የካሪቢያን ሀገራት በራቸውን ለጎብኚዎች ክፍት ማድረግ ጀምረዋል፡፡

ከአስራ ሶስት የካሪቢያን ሀገራት መካከል ኩባ ባርባዶስ ባሃማስ እና ሌሎችም ሀገራት ለቱሪስቶች በራቸውን ክፍት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

እንደዚሁም ላቲቪያ ሉቲኒያ እና ኢስቶኒያም ቱሪስቶች ሀገራቸው እንዲጎበኙ ፈቅደዋል፡፡

በርካታ የአለም ሀገራት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በራቸውን የዘጉ ሲሆን አሁን ግን ለመክፈት እንዳሰቡ ነው የተነገረው፡፡

ሀገራት በራቸውን ለቱሪስቶች ለመክፈት ቢያስቡም የአለም የጤና ድርጅት ግን ሀገራቱን እያስጠነቀቀ ነው የሚገኝው፡፡

ሜክሲኮ እና ታይላንድ ደግሞ በቅርቡ ሀገራቸው ለቱሪስቶች ክፍት ለማድረግ እንዳሰቡም ነው የተነገረው፡፡

የካሪቢያን የውበት ሰገነት የሆኑት ኩራካዎ እና ቦናሪ ከሚቀጥለው ሀምሌ ወር ጀምሮ ከአውሮፓ እና ከካናዳ ቱሪስቶችን ሊያስተናግዱ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

ከአሜሪካ ወደ ካሪቢያን የሚሄዱ ቱሪስቶች ደግሞ ጉብኝት እንዲያደርጉ የተፈቀደላቸው ደግሞ ሀምሌ ወር አጋማሽ ላይ ነው፡፡

ወደ እነዚህ ሀገራት የሚያቀኑ ሁሉም ጎብኝዎች የኮቪድ 19 ምርመራ ያደረጉ እና ውጤታቸውም ኔጌቲቨ የሆኑት ብቻ ናቸው መግባት የሚችሉት፡፡

ታድያ በነዚህ ሀገራት ጉብኝት ለሚያደርጉ ጎብኝዎች ሀገራቱ ሙሉ የጤና ኢንሹራንስ እንዳዘጋጁ ማስታወቃቸውን ሲ ኤን ኤን በጉዞ አምዱ ዘግቧል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *