የጊኒ-ቢሳው ፕሬዝዳንት በድንገት አምስት ሚኒስትሮችን ከስልጣን አሰናበቱ፡፡

የጊኒ-ቢሳው ፕሬዘዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ የመከላከያ ሚንስትሩን እና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትሩን ጨምሮ 5 ሚንስትሮችን ከስልጣናቸው ማባረራቸው ተገልጿል፡፡

የተባረሩት 5ቱም ሚንስትሮች የገዢው ፓርቲ አባልና የፕሬዘዳንቱ ታማኝ ሚንስትሮች ናቸው ተብሏል፡፡

ነገር ግን ፕሬዘዳንቱ ትናንት ማምሻቸውን በቀጭን ትዕዛዝ አልያም ውሳኔ ሚንስትሮቹ ከስልጣን መነሳታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

የሀገሪቱ መንግስት እስካሁን ሚንስትሮቹ የተባረሩበትን ምክንያት ይፋ አላደረገም፡፡

የሚኒስትሮች የሥራ መልቀቂያ ሰኞ ከፓርላማ ስብሰባ በፊት መምጣቱ ጠበቆች የትኛውን የፖለቲካ አጋርነት አገሪቱን የመግዛት መብት እንዳላቸው ይከራከራሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

ዛሬ በጊኒ-ቢሳው ከሚከናወነው አጠቃላይ የፓርላማ ስብሰባ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ለሚኒስትሮቹ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ መስጠት አግባብ አይደለም ሲሉ የሀገሪቱ ጠበቆች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ሊወስዱትና ሊከራከሩ እንደሚችል ይጠበቃል ሲል ሜትሮ ዩ ኤስ ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *