በአዲስ አበባ ሐይሌ ጋርመንት አካባቢ ተበጥሶ የወደቀ የኤልክትሪክ ሽቦ የነካች የስምንት አመት ህጻን ሕይወቷ አለፈ፡፡

በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ሀይሌ ጋርመንት ሰፈራ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ተበጥሶ በወደቀ የአሌክትሪክ መስመር የስምንት አመት ህጻን ልጅ ህይወቷ ማለፉ ተገልጿል።

ተበጥሶ የወደቀው የኤልክትሪክ ሽቦ ከአንድ መኖርያ ቤት ወደ ጎረቤት ለማስተላለፍ ተብሎ የተቀጠለ ነበር ተብሏል፡፡

ህይወቷ ያለፈው ህጻን ልጅ የወደቀውን የኤልክትሪክ ሽቦ በድንገት ለመንካት በሞከረችበት ወቅት ነው አደጋው የደረሰባት፡፡

የአካባው ነዋሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም አንደተናገሩት ከሆነ በተለያዩ ምክንያቶች የኤልክትሪክ መስመሮች በየ ቦታው ተበጥሰው እንደወደቁ ነው የተናገሩት፡፡

ጉዳዩን አስመልክተው ለክፍለ ከተማው የኤልክትሪክ አገልግሎት በተደጋጋሚ ብንደውልም መልስ የሚሰጥ አካል አላገኝንም ሲሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ይህው ዝምታቸው ዛሬ ላይ የስምንት አምት ህጻን ልጅ ህወት አሳጥቷልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አባባ ከተማ የኤልክትሪክ አገልግሎት ሃላፊ አቶ በቀለ ክፍሌ በበኩላቸው ህጻኗ ህይወቷ እንዳለፈ ተናግረው በህጉ መሰረት ጎረቤት ለጎረቤት ኤልክትሪክ መዋዋስ አይፈቀድም ብለዋል፡፡

ያለ አግባብ ከቤት ወደ ቤት የሚተላለፉ ኤሌክትሪክ መስመሮች እንደዚህ አይነት ክስተት ስለ ሚያስተናግዱ ህብረተሰቡ ሊጠነቀቅ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *