በኢትዮጵያ በየጊዜው ለሚከሰተው ቀውስ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት በአጥፊዎች ላይ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ገለፀ፡፡

በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የሚገጥመውን የፅጥታ ችግር እና የዜጎችን የደህነንት ጥያቄ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ፣በአጥፊዎች ላይ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን አስታውቋል።

በሀገራችን ተደጋጋሚ ጥፍቶች የሚቀጥሉት ፣ የአጥፊዎች ተጠያቂነት ማረጋገጥ ሳይቻል ሲቀር መሆኑን ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን ኮምሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ለአትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ህግ በማስከበር እና የአጥፊዎችን ተጠያቂነት በማረጋገጥ በኩል መንግስት ቁርጠኝነቱን አሳያለው ብሏል ይህንንም ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል ኮምሰነር ዶክተር ዳንኤል፡፡
አሁን ከሚታየው አዙሪት ውስጥ መውጣት የሚቻለውም ፣ የአጥፊዎች ተጠያቂነት በማረጋገጥ ብቻ መሆኑን ኮምሽነሩ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል የተለያዩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ድርጅች ፣ አባሎቻችን አለአግባብ ታስረዋል የሚል አቤቱታ ለኮምሽኑ ማቅረባቸውንም ተነግሯል፡፡

በቀረቡ አቤቱታዎች መሰረት እና ከድምጻዊ ሃጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ቀውሶችን ለማጣራት የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ ስራ መጀመሩንን ዶክተር ዳንኤል ተናግረዋል።

በሀገራችን ውስጥ የተለያዩ አስተያየቶች እና አመለካከቶች በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ የመጠየቅ ስርዓት እንዲኖር ዶክተር ዳንኤል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በዳንኤል መላኩ
ሐምሌ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.