የግብፅ ፓርላማ በሊቢያ ጉዳይ ላይ ሀገሪቱ ጣልቃ እንድትገባ ፈቀደ፡፡

የግብፅ ፓርላማ ለፕሬዝዳት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በሊቢያ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዲገቡ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡

ግብፅ ወደ ሊቢያ ወታደሮቿን በመላክ በሀገሪቱ ያሉ ታጣቂ ቡድኖችን ለመዋጋት ነው ከፓርላማው ፍቃድ ያገኘቸው፡፡

በሊቢያ ምስራቃዊ ክፍል የሚንቀሳቀሰው የጦር አዛዡ ካሊፋ ሀፍታር ታጣቂ ቡድን በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ከተሰጠው የሀገሪቱ መንግስት ጋር ውጊያ ከገጠመ ሰነባብቷል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የግብፁ ፕሬዝዳት አል ሲሲ በሀገሪቱ ብሄራዊ ደህንነት ላይ እና በጎረቤቷ ሊቢያ ብሄራዊ ደህንነት ላይ ስጋት የሚጥሉ ጉዳዮች ከገጠሙ ሀገራቸው እጇን አጣጥፋ እንደማትቀመጥ አስጠንቅቀው ነበር፡፡

ቱርክ ካለፈው ወር ጀምሮ በሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ ጉዳይ ላይ ታደርው የነበረውን ድጋፍ ማቆሟን ተከትሎ ግብፅ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትሶች እና ከሩሲያ ጎን በመቆም የጦር አዛዡን ካሊፋ ሀፍታር ቡድንን በመደገፍ ላይ ትገኛለች ሲል ሮይተረስ ዘግቧል፡፡

በያዝነው ወር የካሊፋ ሀፍታር ደጋፊ የሆኑ የሀገሪቱ የፓርላማ አባላት በሊቢያ ጉዳዩ ላይ የግብፅን ጣልቃ ገብነት ጠይቀው እንደነበር ይታወሳል፡፡

በትግስት ዘላለም
ሐምሌ 14 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *