ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ አይነ ስውራን ተማሪዎች የዩንቨርሲቲ መግቢያ በኦላይን እንድንፈተን መወሰኑ ተገቢ አይደለም ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ፡፡

ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ አይነ ስውራን ተማሪዎች የዩንቨርሲቲ መግቢያ በኦላይን እንድንፈተን መወሰኑ ተገቢ አይደለም ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ተፈታኝ አይነ ስውራን ተማሪዎች ስልጠና በአዲስ አበባ በመስጠት ላይ ይገኛል።

የዩንቨርሲቲ መግቢያ ወይም የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን ለመወሰድ ስልጠኛው ላይ የተሳፉ አይነ ስውራን ተማሪዎችም ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ከዚህ በፊት ምንም የኮምፒተር እና የቴክኖሎጂ እውቀት ሳይኖረን በ 5 ሳንምት ስልጠና ብቻ ብሄራዊ ፈተና በኦላይን ተፈተኑ መባሉ ተገቢ አይደለም ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

ከ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጀምሮ ምንም አይነት የቴክኖሎጂ እና የኮምፒተር እውቀት የሌለን አይነ ስውራን ተማሪዎች በወረርሽኙ ምክንያት በኦንላይን እንድንፈተን መወሰኑ ተገቢ አለመሆኑን ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ፣ በበኩላቸው አይነ ስውራን ተማሪዎች በሚኖራቸው የ5 ሳንምት የስልጠና ቆይታ ለፈተና የሚያበቃ መሰረታዊ የኮምፒተር ስልጠና ይሰጣቸዋል ብለዋል፡፡

ስልጠናው አይነ ስውራን ተማሪዎች በራሳቸው ቴክኖሎጂን በመጠቀም ፈተናውን እንዲወስዱ ለማስቻል የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተፈታኝ ተማሪዎቹ ስልጠናውን ከወሰዱ በኋላ ቅሬታ ካላቸው ተጨማሪ ስልጠና ወይም ሌላ መፍትሔዎችን እንደሚፈልጉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በ2012 የትምህርት ዘመን የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከሚፈተኑ ተማሪዎች መካከል 400 የሚሆኑት አይነ ስውራን ተማሪዎች ናቸው።

ሚኒስቴሩም ለእነዚህ 400 ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን መወሰድ የሚያስችላቸውን ስልጠና ለመስጠት ለሁሉም ተማሪዎች ጥሪ ቢያደርግም 250 ተማሪዎች ብቻ ስልጠና ላይ ተገኝተዋል።

በመሆኑም በ2012 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተማሪ የነበራችው አይነ ስውራን ተማሪዎች የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና መፈተን የሚያስችላችሁን ስልጠና እንድትወስዱ ወደ አዲስ አበባ መጥታችሁ ትምህርት ሚኒስቴር ሪፖርት አድርጉ ተብላችኋል።

በዳንኤል መላኩ
ሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *