በተጠናቀቀው 2012 በጀት ዓመት 305 ተሸከርካሪዎችን ገዝቶ ለመንግስት ተቋማት ማስረከቡን የመንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ።

በኤጀንሲው የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ደፊል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በተጠናቀቀው 2012 በጀት ዓመት 305 ተሽከርካሪዎችን ገዝቶ ችግሩ ላለባቸው የፌደራል እና የክልል ተቋማት በጨረታ ገዝቶ ማስረከቡን ተናግረዋል።

የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ያለባቸውን የተሽከርካሪ ችግር ለማቃለል እንዲሁም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሥር ለሚገኘው ሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል በአስቸኳይ ለአገልግሎት መቅረብ ያለባቸው ተሽከርካሪዎችን በመለየት በውስን ጨረታ ግዥ እንዲፈጸም መደረጉም ተገልጿል፡፡

በውስን ጨረታ የግዥ ዘዴ ከዱባይ ሀገር በ6 ምድብ የተሽከርካሪ ዓይነቶች 305 ተሽከርካሪዎችን ከ366 ሚሊዮን በላይ ብር ግዥ መፈጸሙን አቶ መልካሙ ገልጸዋል፡፡

የተሽከርካሪ ግዥ የተፈጸመላቸው የፌዴራል ተቋማት አምቡላንስ ፣ ፒካፕ ፣ ሚኒባስ ፣ ከ 28 ሰው በላይ የሚጭን ኮስትር መኪና እንደሚገኝበትም ተነግሯል፡፡

ለብሄራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት ኤጀንሲ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግዥ ለመፈጸም ከ90 ሚሊየን ብር በላይ ውል መፈረሙንም ከዳይሬክተሩ ሰምተናል፡፡

በዳንኤል መላኩ
ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *