በጀርመን በኮሮና ምክንያት ት/ቤት ከተዘጋ በኋላ የመጀመርያዎቹ ተማሪዎች ትናንት ወደ መማርያ ክፍላቸው ገብተዋል፡፡

በጀርመን ት/ቤቶች መከፈት የጀመሩ ሲሆን በሰሜን ጀርመን ግዛት የሚገኙ ተማሪዎችም ከክረምት እረፍት በኋላ ወደ ሙሉ ሰአት ትምህርት ገበታቸው ሲመለሱ በሀገሪቱ የመጀመርያዎቹ ሆነዋል፡፡

የጀርመን ትምህርት ሚኒስትር አንጃ ካረሊሼክ በትምህርት ቅጥር ግቢ ውስጥ የፊት መሸፈኛ ማስክ ማድረግ አስገዳጅ እንዲሆን ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በትምህርት ቤቶች ውስጥ መሟላት ስላለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች የመጨረሻው ውሳኔ የሚሆነው ግን የክልል መንግስቱ ነው ብለዋል ፡፡

ትምህርት ቤቶች የተወሰኑ ክፍሎችን ሲሰጡ የነበረ ቢሆንም፣ ጥቂቶች ደግሞ በከፊል የተወሰኑ ሰአቶች ለማስተማር ሲሞክሩ የነበረ ቢሆንም በመደበኝነት ሙሉ በሙሉ ሲጀመር ግን ትናንት የመጀመርያው ነው፡፡

አስራ ስድስቱም የጀርመን ክልሎች ሙሉ ሰአት ትምህርት ለመጀመር ተስማምተው ነበር፡፡

በሀምቡርግ ከነገ በስትያ ትምህርት የሚጀመር ሲሆን በበርሊን ደግሞ በሚቀጥለው ሳምንት ይጀመራል ተብሏል፡፡

ላይፕዚሽ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ወረርሽኝ ምንጭ አይሆኑም ሲል ባጠናው መሰረት ነው ጀርመን ት/ቤቶቿን ሙሉ ለሙሉ ለመክፈት የወሰነችው፡፡

በ 2 ሺህ 6 መቶ በሳክሶኒ በሚገኙ ተማሪዎችና መምህራን ላይ በግንቦትና በሰኔ የተደረገው ምርመራ የሚያሳየውም በማንም ላይ ቫይረሱ አለመኖሩን ነው፡፡

በጀርመን የኮሮና ተጠቂዎች 211 ሺህ መድረሳቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሔኖክ አስራት
ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *