በሊባኖስ መዲና ቤሩት ከተማ በትናንትናው ዕለት ፍንዳታ ደርሶ ከ100 በላይ ሰዎችን ሲገድን ከ300 ሺህ በላይ ሰዎችን ደግሞ ቤት አልባ አድርጓል።
በዚህች ከተማ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የሚኖሩ ሲሆን ተጎጂ ኢትዮጵይዊያን ሳይኖሩ እንዳልቀሩ ይገመታል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአደጋው ተጎጂ ኢትዮጵይዊያን ይኖሩ ይሆን? ተጎጂ ዜጎች ካሉስ ሚኒስቴሩ ምን እየሰራ ነው? ሲል ጠይቋል።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ድንገተኛ አደጋዎች ሲደርሱ ለዜጎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት አስቸጋሪ ቢሆንም ቤሩት በሚገኘው ቆንስላ ጽህፈት ቤት አማካኝነት ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረግ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በትህናትናው ዕለት ቤሩት በደረሰው አደጋ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች እንደተጉዱ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከስራቸው የተፈናቀሉ ፣የወር ደሞዝ ያልተከፈላቸው በቆንስላ ጽህፈት ቤት አማካኝነት ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆንንም ተናግረዋል፡፡
በቤሩት ለሚገኙ ዜጎችም ትልቅ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው ብለዋል አምባሳደር ዲና፡፡
ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ዜጎችን እንደመለሱ በማድረግ ሂደት ውስጥ የመመለስ ፍላጎት የሌላቸው ሰዎች መኖራቸውም ችግር እንደሆነባቸውም አምባሳደር ዲና ገልጸዋል፡፡
በዳንኤል መላኩ
ሐምሌ 29 ቀን 2012 ዓ.ም











