በአለማችን በየ15 ሰከንዱ በአማካኝ አንድ ሰው በየቀኑ ደግሞ 6 ሺህ ገደማ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ተገለጸ፡፡


በከፍተኛ ቁጥር ቫይረሱ የተስፋፋባቸው ሀገራት በሚልም አሜሪካ ፤ብራዚል ፤ህንድ እና ሚክሴኮ ቀዳሚ ሆነዋል፡፡

ካለፉት ሁለት ሳምንታት በተገኘው መረጃ መሠረት ሮይተርስ አሰላሁት እንዳለው በየዕለቱ በአማካይ 5 ሺህ 900 ሰዎች በየቀኑ ይሞታሉ ብሏል ሮይተርስ ፡፡

ይህም በሰዓት 247 ሰዎች ይሞታሉ ወይም በየ 15 ሰኮንዶች አንድ ሰው ይሞታል ማለት ነው፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራንፕ አሜሪካ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት አድርጋለች ፡፡

ቢሆንም ብዙ ዜጎቻችን ህይወታቸውን አተዋል ፡፡ይህ ማለት ግን ምንም ስራ አልሰራንም ማለት አይደለም ብለዋል፡፡

ፕሬዘዳንቱ አክሲዮን ከተባለ የዜና ድህረ ገጽ ጋር በነበራቸው ቆይታ “የሆነው ሆኗል …ግን ያ ማለት የምንችለውን ያህል አናደርግም ማለት አይደለም ፡፡ ወረሽኙ አሰቃቂ መቅሰፍት ነው። ” ሲሉ መልሰዋል፡፡

አሁን ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ አውስትራሊያ፤ሆን ኮንግ፤ ቦሊቪያ ፤ሱዳን ፤ቡልጋሪያ፤ ቢልጂየም ፤ ኡዝቤክስታን እና እስራኤል ቫይረሱ በእጅጉ በፍጥነት እየተስፋፋባቸው ያሉ አገራት መሆናቸውን የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያስረዳል።

በያይኔአበባ ሻምበል
ሐምሌ 29 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *