በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የሟቹች ቁጥር ከ700 መቶ ሺህ አለፈ።

መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው ጆንስ ሆፒከንስ ዩኒቨርስቲ እንዳወጣው መረጃ በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 700 ሺህ 647 ደርሷል፡፡

እስካሁን 18 ሚሊየን 54 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 11.13 ሚሊየን ሰዎች ማገገም ችለዋል፡፡

ብራዚል በሚያገግሙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚ ነች ስትሆን በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ከነበሩት 2.8 ሚሊየን ሰዎች መካከል እስካሁን 2.15 ሚሊየን ያህሉ አገግመዋል፡፡

አሜሪካም በሚገግሙ ሰዎች ቁጥር ሁለተኛ ስትሆን 1.5 ሚሊየን ሰዎች አገግመዋል፡፡

በአሜሪካ 4.77 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 156 ሺህ 800 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡

በብራዚል በዚህ ቫይረስ ሰበብ 95 ሺኅ 869 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡

አሜሪካንና ብራዚልን በመከተል በሟቹች ቁጥር ሶስተኛዋ አገር እንግሊዝ ስትሆን 48 ሺኅ 869 ሰዎች ህይታቸው አልፏል፡፡

አሁን በቻይና ምንም አይነት የቫይረሱ ተጠቂ የሌለ ሲሆን በቻይና ኮሮና ቫይረሱ 88 ሺኅ 206 ሰዎችን አጥቅቶ የ4 ሺኅ 676 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፡፡

በዚህች ሀገር ውሃን ከተማ መነሻውን ያደረገው ይህ ቫይረስ በ188 ሀገራት ተሰራጭቶ አሁንም ዜጎች በዚህ ፈውስ አልባ ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው እያለፈ ይገኛል።

በያይኔአበባ ሻምበል
ሐምሌ 29 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *