በቤሩት ለደረሰው ፍንዳታ ቅርበት ያላቸው ባለስልጣናት በቁም እስር ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በሊባኖስ መዲና ቤሩት ከተማ በደረሰው ከባድ ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር ወደ 135 አሻቅቧል።

የሊባኖስ ካቢኔ ለሁለት ሳምንት ያህል በዋና ከተማው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል በተጨማሪም የከተማዋን የደህነት ስራ የጸጥታ ሀይሉ በበላይነት እንዲቆጣጠር መወሰኑ ተሰምቷል፡፡

ከትላንት በስቲያ ከሰአት በቤሩት የደረሰውን ከባድ ፍንዳታ ተከትሎ እስካሁን በተደረገ ፍለጋ 135 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 5 ሺህ ሰዎች ደግሞ የመቆሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡

የመንግስት ባለስልጣት የሟቹች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ገልጸው ፤የነፍስ አድን ስራው ግን አሁንም መቀጠሉን ተናግረዋል ፡፡

የቤሩት የከተማዋ ገዢ እንዳሉት እስከ 300 ሺህ ሰዎች ቤት አልባ ሆነዋል ብለዋል፡፡

ለነዚህ ሰዎች ባለስልጣናት ምግብ ፣ ውሃ እና መጠለያ እንዲያገኙ ለማድረግ እየሰሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል ፡፡

በሌላ ዜና ከፍዳታው ጋር በተገናኘ ምርመራ መንግስት መጀመሩን ቢያሳውቅም ፤ በሌባኖስ ከፍተኛ ቁጣ ተቀስቅሷል፡፡

ከአደጋው ጋር ተያያዞም ቅርበት ያላቸው ባለስልጣናት በቤት ውስጥ እስር እንዲቆዩ መደረጉን ሮይተርስ ዘግቧል።

የፍንዳታው መንስኤ ወዲያውኑ ባይታወቀም ባለስልጣናቱ በደረቅ ወደብ ውስጥ 2.7 ቶን አልሙኒየም ናይትሪት አላግባብ ለስድስት አመታት በመከማቸቱ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *