ክረምት ከመግባቱ ጋር ተያይዞ አዳዲስ የመንገድ ቁፋሮዎች አይከናወኑም ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የክረምት መግባት ጋር በተያያዘ በመንገድ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚካሄዱ አዳዲስ የቁፋሮ ስራዎችን ከግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ማስቆሙን  እና  ለተግባራዊነቱም የክትትልና ቁጥጥር ስራ እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከመንገድ መሰረተ ልማት ጋር ተያይዞ የቁፋሮ ፈቃድ ይሰጥባቸው ከነበሩት ውስጥ የመጠጥ ውሃ ዝርጋታ፣ የዝናብ ውሃ ከድሬኔጅ መስመር ጋር ይገናኝልኝ ጥያቄ፣ የፍሳሽ መስመር ማገናኘትን ጨምሮ የሚከናወኑ ተግባራት እንደሆኑ ተግሯል፡፡

ባለስልጣኑ በክረምት የሚደረጉ ቁፋሮዎች በነዋሪው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ እክል እንዳይፈጥር፣ ከአደጋ ለመጠበቅና የትራፊክ ፍሰት እንዳይስተጓጎል የቁፋሮና የአስፋልት መቁረጥ ፍቃድ መስጠት እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ማቆሙን ገልጿል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2012 በጀት ዓመት በቁጥር 443 የሚሆኑ ከተለያዩ አካላት የቀረቡለትን የመንገድ መቁረጥ ጥያቄ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡

በተጨማሪም የመንገድ ሃብት ላይ ህገወጥ ድርጊቶችን በመፈጸም ጉዳት የሚያደርሱ አካላት ላይ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የመንገድ መብት ጥሰቶችና ጉዳቶች ለመከላከል የሚያስችል አሰራርን በመዘርጋት እየሰራ ይገኛል፡፡

ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *