በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን ተሸገረ፡፡

በአፍሪካ በኮቪድ -19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊየን መሻገሩን የተናገረው መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የጆንስ ሆፒከንስ ዩኒቨርስቲ ነው፡፡

ከዚህ ከተያዙት ግማሽ ያህሉን የያዘችው ደግሞ ደቡብ አፍሪ ናት ብሏል ቢቢሲ ዩኒቨርስቲውን ጠቅሶ፡፡

በርካታ የአፍሪካ ሀገራት አሁን እየመረመሩት ያለው ናሙና አነስተኛ በመሆኑ ነው እንጂ ቁጥሩ ከዚህም ሊያሻቅብ እንደሚችልም ተገምቷል፡፡

በአህጉሪቱ ባሉ ትልልቅ ከተሞች የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑም ተነግሯል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ በአለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 18.6 ሚሊዮን ነው፡፡ ከ702 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል ብሏል።

በአፍሪካ ደግሞ 21ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ሲሞቱ ከ670 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ነሀሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *