ኢየሩሳሌም የህፃናትና ማህበረሰብ ልማት ድርጅት ከ750 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ የ10 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ቀርጾ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን አስታወቀ።

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ ገብሩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ ሲባል ከስዊድን አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ሲዳ) በተገኘ 10 ነጥብ 5 ሚሊዩን ብር ፕሮጀክት መቀረፁን ተናግረዋል፡፡

በተቀረፀው ፕሮጀክትም በአምስት ከተሞች የሚኖሩ ለችግር ተጋላጭ የሆኑ እና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የግንዛበረ ፈጠራ፣ የቁሳቁስ እና ኑሮ መደጎሚያ ገንዘብ ድጋፍ ይደረጋል ተብሏል።

ድጋፉ ከሚደረግባቸው ከተሞች መካከልም በደብረብርሃን፣ባህርዳር፣ቢሾፍቱ፣ቢሻን ጉራቻ እና ሐዋሳ ከተሞች ከ750 ሺህ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች መሆናቸውን ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

የመጀመሪያው ዙር ድጋፍ በደብረብርሃ፣አዲስ አበባ፣ባህር ዳር እና ደብረሲና ከተሞች ለሚኖሩ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ የንጽህና መጠበቂያ፣ምግብ እና መሰል ድጋፎችን አድርጓል።

በቀጣይ ደግሞ ባህርዳር ከተማ ፣ በቢሾፍቱ እና ቢሻን ጉራቻ እንዲሁም በሀዋሣ ከተማ ለቀጣይ 6 ወራቶች የሚዘልቁ ተመሳሳይ ድጋፍችን እንደሚያደርጉ ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

እንደ ሀላፊው ገለፃ ኢህማልድ ለህብረተሰቡ ከሚያደርገው ድጋፉ በተጨማሪ የጤና ተቋማት የኮሮና ወረርሺኝን ለመከላከል ለሚያደርጉት ጥረት ለተቋማቱ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በሳሙኤል አባተ
ነሀሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *