የሆንግ ኮንግ ሚዲያ ባለቤት ጂሚ ሊ በሆንግ ኮንግ ስራ ላይ በዋለው የደህንነት ህግ መሰረት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡
ግለሰቡ የተያዙት ከውጭ ሀይሎች ጋር እየሰራችሁ ነው በሚል ሲሆን ሌሎችም ከፍተኛ ባለስልጣናት በተመሳሳይ እየተከሰሱ ነው ተብሏል፡፡
ቻይና ከአንድ ወር በፊት አዲስ የደህንነት ህግ በሆንግ ኮንግ ካወጣች በኋላ በርካታ ግለሰቦችን ከውጭ ሀይሎች ጋር አብራችኋል በሚል ክስ እንዲመሰረትባቸው ተደርጓል፡፡
ከዚሁ ጉዳይ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ተጨማሪ ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አረጋግቷል፡፡
ተንታኞች እንደሚሉት የ ‹‹ ሊ ›› መታሰር ቻይና የፀጥታ ህጎችን ካወጣች በኋላ በሆንግ ሆንግ የሚንቀሳቀሱ የሰበዓዊ ተማጋቾችን ለማፈራረስ ልትጠቀምበት ትችላለች ብለዋል፡፡
ይህም ከምዕራባውያኑ ለሚሰማው ወቀሳ ትልቅ ማስፈራሪያ ነው ሲሉ ማከላቸውን ዥንዋ ዘግቧል
በሙሉቀን አሰፋ
ነሀሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም
