ሰበር ዜና ሩሲያ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ማግኘቷን አስታወቀች።

የአገሪቱ ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአርቲ የዜና ወኪል ከደቂቃዎች በፊት እንዳስታወቁት ሩሲያ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን አግኝታለች።

ይህንን ክትባትም የሩሲያ ፕሬዘዳንት ፑቲን ሴት ልጅ መከተቧ እና ፈዋሽነቱ መረጋገጡም ተገልጿል።

የሞስኮ ጋማሊያ ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው አዲስ የበለፀገው ክትባት በዛሬው እለት ከሩሲያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እውቅና ማግኘቱን ይፋ አድርጓል፡፡

በቅርቡም የሩሲያ የኮቪድ-19 ክትባት በብዛት ማምረት እንደምትጀምር ፕሬዘዳንቱ ገልፀዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ነሃሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *