ሳይንቲስቶች የአንበጣ መንጋ እንዲፈጠር ምክንያት የሆነውን ኬሚካል ማወቃቸውን አስታወቁ፡፡

በቀን የራሳቸውን ክብደት ያክል የሚመገቡት አንበጣዎች ፤በብዛት ሲሰባሰቡ ሰብል ያወድማሉ፡፡

ከቅርብ ወራት በፊት እንኳ ኢትዮጵያንና ኬኒያን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪቃ ሀገራት ከፍተኛ የሰብል ውድመት አድረሰዋል እንደ ቢቢሲ ዘገባ፡፡

ተመራሪዎቹ ያገኙት አዲስ ግኝት አንዱ አንበጣ ከሌላ አንበጣ አጠገብ ሲሆን የሚያመነጨው መአዛ አለ፡፡

ይህ መአዛ ደግሞ ሌሎችን በመሳብ እንዲሰባሰቡ ያደርጋቸዋል፡፡

እንዲህ እንዲያ እያለ በዚህ መአዛ ምክንያት አንበጣዎቹ ተሰባስበው ወደ መንጋነት ያደጋሉ፡፡

ሳይንቲስቱቹ እንደሚሉት ይህንን መንጋ እንዲፈጠር ምክንያት የሆነውን መአዛ ማሽተት የማይችሉ አንበጦችን በዘረመል ምህንድስና በላብራቶሪ ውስጥ በማራባትና በማውጣት መንጋው እንዳይፈጠር ወይም ደግሞ ፌርሙን (መአዛ) በመጠቀም በቀላሉ በአንድ አከባቢ እንዲሰባሰቡና በቀላሉ እንዲወገዱ ለማድርግ እንዲቻል እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ነሀሴ 7 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *