ሩሲያ የኮቪድ 19 ክትባትን ለአሜሪካ ለማቅረብ ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች፡፡

ይህን የማደርገዉ ግን የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር ስላልቻለች ለማገዝ ያህል ነዉ ብላለች ሩሲያ፡፡

አሜሪካ በበኩሏ ሩሲያ ሰራሹን ክትባት እንደማትፈልግና እንዳዉም በክትባቱ ዉጤታማነት ላይ ጥርጣሬ እንዳላትም ጭምር ገልጻለች፡፡

በአሜሪካ እየተዘጋጀ የሚገኘዉ ክትባት ዉጤት ወደ ተሻለ ደረጃ ደርሷል ያሉት የነጩ ቤተ-መንግስት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኬየሊይ ማክኔኒ፣ሩሲያ ሰራሁት የምትለዉ ክትባት የአሜሪካን ግማሽ ደረጃ እንኳ ያልደረሰ መሆኑን ገልጸዉ እኛ ዜጎቻችንን የክትባት መሞከሪያ የምናደርግበት ምክንያት የለም ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሱ ዘግቧል፡፡

የሩሲያ ባለስልጣናት ለሲ ኤን ኤን እንዳሉት፣አሜሪካ ሩሲያ ሰራሽ ሆነዉን ሁሉ ሁሌም በጥርጣሬ እንደምትመለከት ገልጸዉ፣ይህ ግን የህይወት ጉዳይ በመሆኑ ክትባቱን በመጠቀም ለዜጎቿ ልትደርስ ይገባል ብለዋል፡፡

ሩሲያ በዓለም ላይ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል መወሰኗን ተከትሎ በርካታ ሀገራት ክትባቱን በእጃቸዉ ለማስገባት ፍላጎት ማሳየታቸዉ ተነግሯል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
ነሀሴ 8 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *