እንግሊዝ ከፈረንሳይና ኔዘርላንድ ወደ አገሯ የሚመጡ ሰዎችን ለ14 ቀናት ወደ ለይቶ ማቆያ እንምታስገባ አስታወቀች፡፡

የሃገሪቱ የትራንስፖርት ሃላፊ ግራንት ሻፖስ ለቢቢሲ እንዳሉት፤ሀገራቸዉ ይህን እርምጃ ለመዉሰድ የተገደደችዉ እየጨመረ የመጣዉን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል በሚል ነዉ፡፡

የፈረንሳይ መንግስት በበኩሉ በእንግሊዝ ዉሳኔ ቅር መሰኘቱን ገልጾ ከእንግሊዝ ወደ ፈረንሳይ በሚጓዙ ሰዎች ላይም ተመሳሳይ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡

የእንግሊዝን ዉሳኔ የራሷ ዜጎች ሳይቀር እንደተቃወሙት የጠቀሰዉ ዘገባዉ፤በአሁኑ ወቅት ከግምሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ እንግሊዛዊያን ፈረንሳይ በጉብኝት ላይ እንደሚገኙም ጨምሮ ገልጿል፡፡

በፈረንሳይ የእንግሊዝ አምባሳደር ሌሊዌሊን፣ሀገራቸዉ የወሰደችዉ እርምጃ ለእንግሊዝም ጭምር መልካም ባይሆንም ግን የዜጎችን ደህንነት ከመጠበቅ የበለጠ ሃላፊነት እንደሌለ በመግለጽ እርምጃዉን ደግፈዉታል፡፡

እንግሊዝ ጎረቤቶቿን ቅር ያሰኘውን ይሄንን እርምጃ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደምታደርግ አስታውቃለች።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ነሀሴ 8 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *